Banner

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3photo Title 5
There are no translations available.

ስልጣንና ተግባር

የአብክመ ፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 74/2003 ራሱን የቻለ ህጋዊ ሰውነት ያለው ክልላዊ ተቐም ሲሆን የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት አሉት፡፡

1.በስራ ላይ ያሉ ህግጋትና ደንቦችን ለማሻሻል የሚያስችሉ የጥናትና ምርምር ፕሮግራሞችን ይነድፋል ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

2.የክልሉን የፍትህ ስርአት የተመዋላ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦችን ያመነጫል፡፡

3.የፍትህ አካላት የዕለት ከዕለት ስራዎችን ለማቀላጠፍና ራሳቸውን ለተገልጋዩ ተደራሽ ለማድረግ የሚያግዙ የህግ ሙያ ስልጠና ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

4.በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርትና ስልጠና ተቐማት ጋር የስራ ግንኙነቶችን ያደርጋል ልምዶችን ይለዋወጣል፡፡

5.በክልሉ የፍትህ አካላት ውስጥ በዳኝነት በዐቃቢ ህግነት በተከላካይ ጠበቃነት በሬጅስትራርነትና በሌሎች ከፍትህ ስርአቱ ጋር ተዛማጅነት ባላቸው የሙያ መስኮች ስርአቱን ለሚቀላቀሉ አዳዲስ የህግ ባለሙያች የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የቅድመ ስራ ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡

6.በክልሉ የፍትህ አካላት ውስጥ በመስራት ላይ ለሚገኙ ዳኞች ዐቃቢያን ህግ ተከላካይ ጠበቆች ሬጅስትራሮችና ሌሎች ከፍትህ ስርአቱ ጋር ተዛማጅነት ባላቸው ሙያዎች ውስጥ በማገልገል ላይ ላሉ የህግ ባለሙያዎች በቃታቸውን ለማሳደግ የሚረዱና ቀጣይነት ያላቸው የስራ ላይና ቅድመ ስራ ስልጠናዎችን በራሱ ወይም ከልዩ ልዩ ከፍተኛ የትምህርትና ስልጠና ተቐማት ጋር በመተባበር ይሰጣል እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

7.ስልጠናዎችን በራሱ ወይም ከልዩ ልዩ ከፍተኛ የትምህርትና ስልጠና ተቐማት ጋር በመተባበር ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ የደርጋል፡፡

8.የሰልጠና ማቴሪያሎችን ህግ ነክ መረጃዎችንና የጥናትና ምርምር ውጤቶችን አዘጋጅቶ ያሳትማል ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ያሰራጫል፡፡

9.የፍትህ ስርአቱን ዋና ዋና ችግሮች ከመንስኤዎቻቸው ጋር በማጥናት በምርምር የተደገፉ የመፍትሄ ሃሳቦችን ያመነጫል እነዚህኑ ጉዳዩ ለሚመለከተው የመንግስት አካል በማቅረብ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ጥረት ያደርጋል፡፡
10.የራሱን የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች ስርአተ ትምህርት አዘጋጅቶ ለቦርድ በማቅረብ ያፀድቃል ሲፈቀድለትም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

11.ራሱ የሚሰጣቸውን ስልጠናዎች የሚመጥን የምስክር ወረቀት ያዘጋጃል ይሰጣል፡፡

12.በትይዩ ከሚገኙ መሰል የፌደራልና የክልል ተቐማት ጋር በመተባበር የህግ ስርአት ጥናት ምርምርና ስልጠና ያከናውናል፡፡

amhara justice proffessional training and legal Research Institute ©2011. All rights reserved